ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በብዙዎች ተደራሽ ለመሆን በሚፈልጉ እንዲሁም የንግድ ስራቸውን በኦንላይን አማካኝነት ለማሳደግ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ዲጂታል ማርኬቲንግ ዋነኛ መሳርያ ሆኗል።ከ 115ሚልዮን በላይ ህዝብ ያላት እና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለችው ኢትዮጵያ ለሁሉም አይነት ንግዶች በርካታ አጋጣሚዎች የምትሰጥ ሀገር ናት።በዚህ ጽሁፍ ላይ ዲጂታል ማርኬቲንግ በኢትዮጵያ ያለበትን ሁኔታ እንቃኛለን እንዲሁም በኦንላይን ንግዳቸውን ማሳደግ ለሚፈለጉ የንግድ ስራዎች ጠቃሚ ምክሮችን እንመለከታለን።
ዲጂታል ማርኬቲንግ በኢትዮጵያ ያለበት ሁኔታ
በኢትዮጵያ ዲጂታል ማርኬቲንግ አዲስ የገበያ አማራጭ እንደመሆኑ መጠን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ዘዴዎችን በመላመድ ሂደት ላይ እንገኛለን።ይሁን እንጂ የኢንተርኔት እድገትና የዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የንግድ ስራዎች ከደንበኞቻቸው ጋር በኢንተርኔት አማካኝነት ለመገኛኘት አዳዲስ አጋጣሚዎችን ይከፍትላቸዋል። ዊ አር ሶሻል ኤንድ ሁትስዊት ባወጣው መረጃ መሠረት በ 2020 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 18 በመቶ ጨምሯል። በአጠቃላይ የተጠቃሚዎቹን ቁጥር ከ22 ሚልዮን በላይ ይሆናል። ይህም የፔኒትሬሽን ሬትን 19በመቶ እንዲሆን ያደርገዋል።ይህ ቁጥር ደግሞ በዘርፉ ገና ብዙ እድገት ማድረግ እንደሚችል ያሳያል።
በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች ውስጥ አንዱ በደንበኞች ፍላጎት፡ በሃሪ እንዲሁም በኦንላይን ላይ በሚቀርቡ የተለመዱ ሀሳቦችን በተመለከተ አስተማማኝ መረጃዎች አለመኖራቸው ነው።የተቀመጡ መረጃዎች አለመኖራቸው የንግድ ስራዎች የኦንላይን ማርኬቲንግ ዘዴዎቻቸውን ለመወሰን ከባድ ያደርግባቸዋል። ይሁንና ልናስብባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች አሉ።
1. ለሞባይል ስልክ የሚስማማ አቀራረብ
አብዛኞቹ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት የሚጠቀሙት በሞባይል ስልካቸው ላይ ነው።የንግድ ስራዎች ዲጂታል ማርኬቲንግን ሲጠቀሙ በሞባይል ስልክ ላይ የሚኖረውን ገጽታ ታሳቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይህም ማለት የሚጠቀሟቸው የሞባይል ድረ ገጾች በሞባይል ለመጠቀም ቀላል ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህም በተጨማሪም በኢንተርኔት ላይ የሚጠቀሟቸውን የማስታወቂያ ዘመቻዎች ለሞባይል ስልክ የተመቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
2. የማህበራዊ ሚዲያ የበላይነት
እንደ ፌስቡክ እና ትዊተር ያሉ የማህበራዊ ሚድያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ተወዳጅ የሆኑ የኢንተርኔት መድረኮች ናቸው። ዊ አር ሶሻል ኤንድ ሆትስዊት ባወጣው መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ ቋሚ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አሉ። ይህም የንግድ ድርጅቶች በማህበራዊ ሚድያ አማካኝነት ከደንበኞቻቸው ጋር ለመገናኘት የሚያስችል ሰፊ አጋጣሚ ነው።
3. በአካባቢው የተለመደውን ቋንቋ መጠቀም
ኢትዮጵያ ከ80 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። የንግድ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ተደራሽ ለመሆን የሚያዘጋጁት ሃሳብ ተደራሽ በሚሆኑባቸው አካባቢዎች የተለመደውን ቋንቋ የሚጠቀም መሆን ይኖርብርታል። ይህም ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲግባቡ እንዲሁም የደንበኞቻቸውን እምነት እንዲያተርፉ ይረዳቸዋል።
የዲጂታል ማርኬቲንግ ዘዴን ለማሳዳግ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች
አሁን ዲጂታል ማርኬቲንግ በኢትዮጵያ ያለበትን ሁኔታ ተመልክተናል።ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የንግድ ስራዎች ንግዳቸውን ኦንላይን ላይ ለማሳደግ የሚረዱዋቸውን አንዳንድ ሃሳቦች እንመልከት።
1. ለሞባይል ስልክ የሚስማማ ድረ ገጽ ማዘጋጀት
አብዛኞቹ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት የሚጠቀሙት በስልካቸው ላይ በመሆኑ ለሞባይል ስልክ የሚስማማ ድረ ግጽ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ለሞባይል ስልክ የሚስማማ ድረ ገጽ ፡ በትንሽ ስክሪን ላይ በቀላሉ የሚታይ ፡ እንዲሁም ፈጣን ባልሆነ ኢንተርኔትም ጭምር ደረገጹን መክፈት የሚቻል ሊሆን ይገባል።
2. Optimize Local SEO
ሎካል ሰርች ኢንጂን ኦፕቶማይዜሽን(SEO) ድረ ገጽዎ በአካባቢዎ በሚደረጉ የፍለጋ ውጤቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲታይ የሚያመቻች ሂደት ነው። ይህንንም ለማድረግ ድረ ገፅዎ፡ በአካባቢዎ ለፍለጋ የሚውሉ ቁልፍ ቃላትን ማካተት ይኖርበታል። ጎግል ማይ ቢዝነስ ሊስቲንግ፥ እንዲሁም ቢዩልዲንግ ሎካል ሳይቴሽንን በመጠቀም ደረገፅዎን በአካባቢዎ ከሚደረጉ የፍለጋ ውጤት ዝርዝሮች መካከል ከፍ ያለ ደረጃ እንዲያገኝ ማድረግ ይችላል።
3. ማህበራዊ ሚድያን መጠቀም
ቀደም ብለን እንደተመለክትነው በኢትዮጰያ ማህበራዊ ሚድያ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መድረክ ነው ።የንግድ ስራዎች አሳታፊ የዘት ያላቸውን ሀሳቦች በማህበራዊ ሚድያ በማጋራት፡የታሰበባቸውን ማስታወቂያዎች በማስተላለፍ እንዲሁም ከደንበኞቻቸው ጋር በኦንላይን ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር በማህበራዊ ሚድያ ላይ ተቀባይነት ማግኘት ይችላሉ።
4. ለሚያዘጋጁት ሃሳብ በአካባቢው የሚነገር ቋንቋን መጠቀም
ለማስተላለፍ የሚፈልጉትን ሀሳብ በሚሰሩባቸው ክልሎች ውስጥ በሚነገሩ ቋንቋዎች ማዘጋጀት በደንበኞች ዘንድ ተአማኒነት ለማግኘት ይረዳል።በአካባቢው የሚነገረውን ቋንቋ መጠቀም የንግድ ስራዎች የደንበኞቻቸውን ፋላጎት እንደተረዱ እንዲሁም ለደንበኞቻቸው ፍላጎት ትኩረት እንደሚሰጡ ያሳያል።
5. የክፍያ ማስታወቂያዎች ላይ ገንዘብን ማዋል
አንደ ፌስቡክ ቲውተር እና ጎግል ባሉ የማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የተከፈለባቸውን ማስታወቂያዎች ማሳየት የንግድ ስራዎች ለብዙ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆኑ እንዲሁም ስዎችን ወደ ድረገጹ ለመሳብ ይረዳቸዋል።ነገር ግን ማስታወቂያው ለሚገባው ሰው እየደረሰ መሆኑን በጥንቃቄ ማጤን ያስፈልጋቸዋል።
Hello, please I want to start job on digital marketing and so i am the beginner.please help me!!